የንባብ ግዜዎን የተሻለ ያድርጉ
ግዜ እና ቦታ በማይገድበው የ ሀሁ ዲጂታል መተግበርያ የንባብ ባህሎን ከምንም ግዜ በላቀ ማሳደግ ይችላሉ።

ለምን እኛን ይመርጣሉ
የርሶን ፍላጎት ያማከለ
ሚወዱትን መፅሀፎች በመምረጥ በመግቢያ ገፆ ላይ ተመሳሳይ መፅሀፎችን ያግኙ።
ለወዳጅ ዘመድ ሚጋብዙት
ከግል ንባብ አንስቶ ለልጆ መማርያ ሚሆኑ እና ለወዳጅ ዘመድ ሚያጋሩት ታላላቅ መፅሀፍቶች ስብስብ የያዘ።
ካቆሙበት ይቀጥሉ
ሚወዱትን መፅሀፍ ቡክማርክ በመጠቀም መተግበርያውን ዘግተው በሚከፍቱ ግዜ ካቆሙበት መቀጠል ያስችሎታል።
አዝናኝ እና ያልተገደበ አገልግሎት
በንባብ መዝናናቶ እንዳይስተጏጎል ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጭም ቢሆኑ ሚፈልጉትን መፅሀፎች ቀድመው በማውረድ ማንበቦን ይቀጥሉ
ታላላቅ የትረካ መፅሀፎች
በስራ በተወጠረ ኑሮ ላይ ሆኖ ማንበብያ ግዜ ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል። በሀሁ eBooks ፖድካስት ሁሉንም ያድምጡ
የአእምሮ ምግብ
የንባብ ባህሎን በማሳደግ የ ሀሁ eBooks ቡፌ ላይ የሚቀርቡ መፅሀፍቶችን እና ትረካዎችን ማእድ ይካፈሉ።

በሁለት አማራጭ የቀረበ
በኦንላይን እና ያለ ኢንተርኔት ግንኙነት የሚሰራ
መተግበርያችን እጅግ ለየት ከሚያረገው ባህሪው አንዱ ሚፈልጉትን መፅሀፍ በኦንላይን ማንበብ ሚያስችል ሲሆን ቀድመው ወደስልኮ በማውረድ እዛው መተግበርያው ላይ ኢንተርኔት አገልግሎት ቢቇረጥቦት ያለ ምንም ችግር ማንበብ ያስችላል።
- ያልተገደበ አገልግሎት
- ሚወዱትን ፀሀፊ ይከተሉ
- ስላነበቡት መፅሀፍ የግል አስተያየቶን ያኑሩ
ዘመናዊ የፖድካስት ማጫወቻ
እጅግ ዘመናዊ የፓድካስት ማጫወቻ
በእንቅስቃሴ ላይ ሆነውም ይሁን ወይም አረፍ ብለው በዩትዩብ ላይ ሚፈልጉትን ፓድካስቶች ለመስማት ሞክረው ያቃሉ? ዩትዩብ እና መሰል ቻናሎች የፊት ገፅታቸውን ዘግተው ወደ ሌላ አፕሊኬሽን ቢሄዱ የከፈቱት ፓድካስት ወድያው ይቇረጣል። ነገር ግን ሀሁ ዲጂታል በሚጠቀመው እጅግ ዘመናዊ የ ድምፅ ኮዴክ ፊውቸር አማካኝነት የእኛ መተግበርያ ላይ ሚፈልጉትን ፓድካስት ከከፈቱ በሃላ ከመተግበርያው ውጭ ፓድካስቱ ሳይቇረጥ ሌላ የግል ስራዎን ስልኮላይ እንዲሰሩ ያስችላል!
- ያልተቇረጠ አገልግሎት
- ሚወዱትን ፓድካስት ይከተሉ
- ስለሰሙት ትረካ የግሎን አስተያየት ያኑሩ






