ከ ሀሁ ዲጂታል በስተጀርባ ያሉትን ይተዋወቁ ሀሁ eBooks ወይም ሀሁ ዲጂታል በሁለት ግለሰቦች መስራችነት የተቇቇመ ሀገራዊ መተግበርያ ነው። ያግኙን እራያችን ቁጥር 1 የዲጂታል መፅሀፍት ምንጭ መሆን አሁን በምንገኝበት የዲጂታል ዘመን ብዙ የሀገራችን የኪነጥበብ ስራዎች በዲጂታል ሚዲያው በመሰራጨት ላይ ይገኛል ነገር ግን የጥበብ እና እውቀት ምንጭ የሆኑ የሀገራችን መፅሀፎች በተቀናጀ እና በአንድ ማእከል ምናገኝባቸው ፕላትፎርሞች አናሳ በመሆኑ ይህን እጥረት ለመቅረፍ በመስራት ላይ እንገኛለን። እቅዳችን ላጠቃቀም ቀላል እና ምቹ የሆነ የዲጂታል ላይብረሪ መገንባት በቅርብ ግዜ የተጀመሩ የ ዘመናዊ ላይብረሪ ግንባታዎች አበረታች ቢሆኑም አገልግሎታቸው ግን በተገነቡበት አካባቢ ላይ የተወሰነ ነው። ስለሆነም ድርጅታችን ይህን የቦታ ውስንነት ይቀርፋል ብሎ ያመነበትን ድንበር አልባ የዲጂታል ላይብረሪ ሰርቶ ለእናንተ ሲያቀርብ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል። እርሶን የሚያስቀድም ሀሁ ዲጂታል የእርሶን የማንበብ ባህል ለማሳደግ እና ፍላጎቶን ለሟሟላት በየቀኑ አዳዲስ መፅሀፍቶችን እና ትረካዎችን ለናንተ ለውድ ደንበኞቻችን ያቀርባል። የሀሁ ዲጂታል መስራቾች ዳዊት ለገሰ መስራች እና አፕሊኬሽን ዴቨሎፐር ሰላማዊት አስናቀ ማርኬቲንግ ማኔጀር